ስለ Hasab

ከሶስት ዓመታት በፊት ሶሻል ሚድያ ማርኬቲንግ ጀመርኩ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከ60 በላይ ቢዝነሶች ጋር ሰርቻለሁ፣ እንዲሁም ከ150,000 በላይ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንዲያድጉ ረድቻለሁ።

የተማርኩት ነገር ቢኖር፦ የሶሻል ሚድያ ጨዋታ ቢዙ ባወቀ ሳይሆን እስክንረዳው ድረስ ብዙ ጊዜ ማፍሰስ ነው። የሚያሸንፉት ሰዎች በትክክለኛው ሀሳብ፣ በትክክለኛው ሁክ፣ በትክክለኛው ጊዜ እና ቦታ በተደጋጋሚ የሚታዩት ናቸው።

አብዛኞቹ የቢዝነው ባለቤቶች ደሞ ያ ሚፈሰው ጊዜ የላቸውም። Hasab የተፈጠረው በዚህ ምክንያት ነው።

Hasab ላንተም ላምቺም ነው ፦

  • ራስዎን «ክሬቲቭ» ብለው ባያስቡም ንግድዎ እንዲያድግ የሚፈልጉ ከሆነ
  • ጥሩ ሀሳብ ሲሰጥዎት መስራት የሚችሉ፣ ግን ሀሳብ ለማምጣት ጊዜ የሌለዎት ከሆነ
  • ኤጀንሲ የሚያንቀሳቅሱ እና ለእያንዳንዱ ደንበኛ አዲስ ይዘት ማምጣት እያደከመዎት ከሆነ

ከላይ ያለው የሚገልጽዎት ከሆነ፣ Hasab የተሰራው ለእርስዎ ነው።

ማነኝ እኔ ምያምኑኝ?

በ19 ዓመቴ የራሴን 1 አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 100,000 ተከታይ ልደርስ ችያለው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የንግድ ባለቤቶች ተመሳሳይ ውጤት እንዲያገኙ ረድቻለሁ — ያንን እንዳሳካ የረዳኝን ሚስጥር Hasab እነሆ ይሎታል። Hasab ተራ AI አይደለም። እኔ ራሴ በየቀኑ የምጠቀምባቸው ስልቶች ትጨምቆ ነው.

በዚ ሳምንት ምን ፖስት ላርግ ብሎ ማሰቡን ይተዉትና። ለHasab መሪውን ይስጡት፤ ካሰቡበት ያደርሶታል።

Need help?